| « የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀጳጳስ አቡነ ሣሙኤል እና አቡነ ጢሞቲዎስ ከኃላፊነታቸው ታገዱ | Samuel T Michael "Melkamneh" (Video) » |
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቅ/ሲኖዶሱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ላይ ጦርነት ከፈቱ (ደጀ ሰላም)
ደጀ ሰላም: ከሮም ጣሊያን ጉብኝታቸው ባለፈው ረቡዕ ወደ አዲስ አበባ የተመለሱት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ መጓዛቸውን ተቃውሞ ደብዳቤ የጻፈባቸው የቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ አስፈጻሚ ላይ “ጦርነት መጀመራቸውን” የአዲስ አበባ ምንጮቻችን ገለጹ።
ለጂ-8 ጉባዔና ለ”ኢትዮጵያ ቀን” ዝግጅት ሮም የሰነበቱት ፓትርያርኩ በራሳቸው ፈቃድ ካደረሱት ጉዞ በተመለሱበት ዕለት የአዲስ አበባ ሊቃውንት ከ6ኤ.ኤም ጀምረው ተሰልፈው
እንዲጠብቋቸው የተደረገ ሲሆን ተቃዋሚዎቻቸው የተባሉ ብፁዓን አባቶችንና ዜናዎች ያወጡ ጋዜጦችን የሚሰድቡ ዘለፋ አዘል “ቅኔዎች” ሲቀርቡ ተሰምቷል። በብዙ ሚሊዮን ብር የሙስና ተግባር ከተራ ግለሰብነት ወደ ሀብታምነት ተሸጋግሯል በሚባለው በወንድማቸው ልጅና የቤተ ክርስቲአን ሕንጻዎችን በትንሽ ገንዘብ በመከራየት መልሰው በብዙ ትርፍ በማከራየት ሀብት በማግበስበስ ላይ ናቸው በሚባሉት በወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ አስተባባሪነት በነቂስ እንዲወጡና ፓትርያርኩን እንዲቀበሉ የተደረጉት ሊቃውንቱ “ከርስዎ ጋር ነን” የሚል መልእክት እንዲያስተላልፉ መገደዳቸውን ምንጮቻችን ዘግበዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቅ/ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከወደቀችበት የሙስናና የዘረኝነት አዘቅት ወጥታ የተሰጣትን ሐዋርያዊ አገልግሎት ለመፈጸም ትችል ዘንድ አንድ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ማቋቋሙ የሚታወስ ሲሆን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብት በመዝረፍ ላይ የሚገኙ ወገኖች ከሚቴው ሥራውን እንዳይጀምር ከፍተኛ ዘመቻ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የዚህ ፀረ-ሲኖዶስና፣ ፀረ ብፁዓን አባቶች እንቅስቃሴ መሪ ናቸው የሚባሉት የጥንቷ የአርቲስት መሐሙድ አሕመድ ባለቤት፣ የዛሬዋ የፓትርያርኩ አወዳሽ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ሲሆኑ ወ/ሮዋ አሜሪካን ሀገር በሚዘጋጀው በሀገር ፍቅር ራዲዮ ሳይቀር ቃለ ምልልስ በመስጠት የአባቶችን ክብር በመጋፋት ላይ ይገኛሉ። ይሄው ፀረ-ሲኖዶስ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ሐሙስ ዕለት የመላው አዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ያለ ሀ/ስብከቱ ዕውቅና ተሰብስበው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባል የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልንና የኮሚቴው ሊቀመንበር የሆኑትን የ ቅ/ሥላሴ ዲን ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስን እንዲያወግዙ ሲነገራቸው ውሏል። የስብሰባው ጥሪ ሕጋዊ እንዳልሆነ የተነገራቸው አስተዳዳሪዎች በስብሰባው ሳይገኙ ሲቀሩ የፓትርያርኩን ብቀላ ፈርተና ል ያሉና በዝምድናና በጥቅም ተሿሚነት የሚታወቁ ምንደኞች ደግሞ በሥፍራው በመገኘት ሲያሟሙቁ መዋላቸው ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሮም ጉብኝታቸው ቤኔዲክት 16ኛን ያገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ታቦተ ሙሴን በሙዚየም አስቀምጬ ለዓለም አሳያለሁ ማለታቸውን “ወርልድኔት ዴይሊ” የተባለ የዜና ተቋም መዘገቡ ታውቋል። ዛሬ አርብ ታቦተ ጽዮንን እንደሚያሳዩ መናገራቸው የተጠቀሰው ፓትርያርኩ ራሳቸውም ታቦተ ጽዮንን እንዳዩ ተናግረዋል ተብሏል። ዜናው በታዋቂ ዓለማቀፋዊ የዜና አውታሮች ያልተዘገበ ሲሆን ነገሩን በብቸኝነት ያቀረበው “ወርልድኔት ዴይሊ” ብቻ ነው። ዜናው ትክክለኛ ይሁን ወይም ሆን ተብሎ የፓትርያርኩን ስም ለማጉደፍ የተደረገ ወደፊት የሚታወቅ ይሆናል።
Related Story:- የቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የቅዱስ ፓትርያርኩን ጉብኝት ተቃወመ(ደጀ ሰላም )
ደጀ ሰላም:- የቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የቅዱስ ፓትርያርኩን ጉብኝት ተቃወመየቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የቅዱስ ፓትርያርኩን ጉብኝት ተቃወመ
በግንቦት 2001 ዓ.ም የቅ/ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ የተመረጠው አዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ቅዱስ ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያለ ቅ/ሲኖዶስ ፈቃድ ወደ ውጪ ለጉብኝት መሄዳቸውን በመቃወም ደብዳቤ መጻፉ ተሰማ። “በጂ-8 በሚካሄደው የተለያዩ ሀገራት የሃይማኖት መሪዎች ስብሰባ ላይ እንዲገኙ” የጣሊያኑ ፕሬዚደንት ባቀረቡላቸው ጥሪ እንዲሁም “የኢትዮጵያ ቀን በዓል ላይ ለመገኘት ወደ ጣሊያን” የተጓዙት ቅዱስ ፓትርያርኩ ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ “የፓትርያርኩ ማንኛውም ጉዞ በቅ/ሲኖዶስ ዕውቅና” እንዲሆን ማለቱን ከግምት ውስጥ አለማስገባታቸውን በመንቀፍ እንደጻፈላቸው ምንጮቻችን ገልጸዋል።
በርግጥም ሥራ አስፈጻሚው የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ ለማስከበር ቆርጦ ከተነሣና የተባለውን ደብዳቤ ከጻፈ እርምጃው በቅርብ ጊዜ የቤተ ክርስቲአኒቱ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ለውጥ ሊአስብል አንደሚያስችል ሐሳባቸውን እንዲያካፍሉን የጠየቅናቸው አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።
ከዚህም በተጫማሪ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ያለምንም መመሪያና ደንብ ለቤተ ክርቲያኒቱ የልማት ኮሚሽን ሥራ አስኪያጅነት ሊፈጸም የነበረውን ቅጥር ሕግ ያልጠበቀ ነው በማለት ቅጥሩ እንዳይፈጸም ደብዳቤ መጻፉም ታውቋል። የኮሚሽኑን የበላይ ሥልጣን የሚይዘውን ሰው ለመቅጠር ያለምንም መስፈርት መጠቀም አዲስ አለመሆኑን የገለጹት ምንጮቻችን “አይሆንም፣ ትክክል አይደለም” ሲባል ግን ይህ የመጀመሪያው ነው። ላለፉት ዓመታት ቦታውን በሃላፊነት ይዘው ይሰሩ ለነበሩት ግለሰብ ከ15 ሺህ ብር በላይ የኢትዮጵያ ገንዘብ ይከፈላቸው እንደነበረና ይህም በወቅቱ ቅሬታ አስነስቶ እንደነበር ይታወቃል።
Trackback address for this post
Trackback URL (right click and copy shortcut/link location)