| « Review:- Gospel Singer Dereje Kebede pessimistic view shadow new album (By Endale Besher) | Have Your Say : Dereje's kebede new message would it hurt or help? » |
የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በአሳዛኝ ሁኔታ ተበተነ (ደጀ ሰላም)
ደጀ ሰላም: ቅዱስ ሲኖዶሱ ያረቀቀውን ቃለ ጉባዔ ሳያጸድቅ፣ የጀመረውን አጀንዳ ሰይቋጭ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሜዳ ላይ ጥሎ ወደ ቤቱ ገብቷል። ከስምምነት ላይ የተደረሰበት ውሳኔ በፊርማ እንዳይጸድቅ ብፁዓን አበው እስጢፋኖስ፣ ኤጲፋንዮስና ጎርጎርዮስ የሞት ሽረት ትግል አድርገው፣ አባቶችን በጥብጠው ውሳኔው እንዲከሽፍ አድርገዋል። በተለይም በምዕራብ ኢትዮጵያ በጀመሩት መልካም አገልግሎት በሕዝቡ እየተመሰገኑ የነበሩት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ይህንን ገዳይ አቋም እንዴት ሊይዙ እንደበቁ እንቆቅልሽ ሆኗል። ገሚሱ በገንዘብ ተገዝተው ነው ሲል ሌላው ደግሞ ውስጠ ዘ በሆነ ማስፈራሪያ ሊሆን ይችላል እያለ ነው።
Photo:- Holy Synod of the Ethiopian Orthodox Tewahedo church
ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ አሸናፊነቱ እየመጡ ያሉት ፓትርያርኩ የበቀል በትራቸውን እንደሚመዙ እየተጠበቀ ነው። የመጀመሪያ ተጠቂዎች የሚሆኑት በአዲስ አበባ የሚገኙ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ሲሆኑ ባለፈው ሳምንት በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል መሪነት ስብሰባ ካደረጉ በሁዋላ የፓትርያርኩን ድርጊት የሚቃወም መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል። ከዚህም ባሻገር ይህንን ሁሉ ሕዝብ ያስተባብርብኛል ያሉት ማህበረ ቅዱሳንም ላይ ጥርሳቸውን ነክሰዋል ተብሏል።
የቤተ ክህነቱ ድራማ ዛሬ ሲተወን ጠዋት በማለዳው ስብሰባ እንዳይገቡ የታገቱት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ለምን እንደታገቱ ፌዴራል ፖሊስ ራሱ አያውቅም። የደህንነት ክፍሉ ደግሞ ለደህንነታቸው ብዬ ነው ብሏል። ድራማው ሊቀ ጳጳሱን ከስብሰባው በማስቀረት ውሳኔውን ማክሸፍ ከሆነ በርግጥም ዘዴው ሰርቷል ማለት ይቻላል።መንግሥት በበኩሉ ጉዳዩን እያጠናው እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ገልጸዋል።
በተያያዘ ዜና ፓትርያርኩ የተነሣባቸውን ተቃውሞ ለመስበርና አባቶችን አንገት ለማስደፋት የሚሆን ገንዘብ ራሳቸው በግላቸው ከሚያዙበት ከቁልቢ ገብርኤል ካዝና ወጪ መደረጉ ታውቋል። የብሩ መጠን ለጊዜው ባይታወቅም ገንዘቡ ለአንዳንድ የፖሊስ ሃላፊዎች፣ ደህንነቶችና ጉልበት ላላቸው ሰዎች መበተኑ ሲታወቅ መንግሥት በውስጡ ሌላ መንግሥት ያለበት አስመስሎታል። እስከ ዛሬም በመንግሥት ስም ቤተ ክርስቲያኒቱን እግርተወርች አስረው ሲበሏት፣ ሲግጧትና ሲያዋርዷት የነበሩ ሰዎች የፓትርያርኩ ዘመዶችና ወዳጆች ብቻ ሳይሆኑ በመንግሥት ሥልጣን ላይ የተንፈራጠጡ ሰዎችም መሆናቸው እየተገለጸ መጥቷል። መንግሥት ጉዳዩን አጣርቶ ሕገ ወጦቹ እጃቸውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እንዲያነሱ ያደርጋል ተብሎ ይገመታል።
ነገሩ በዚህ ከቀጠለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ አላት ለማለት እንደማያስደፍር አንድ ሊቀ ጳጳስ ተናግረዋል። ከዋሺንግተን ዲሲ ተጠርተው የተሾሙት የሲዳሞ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሥራ አስፈጻሚው አባል ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልም በበኩላቸው “ሀ/ስብከቴን ተረከቡኝ” ማለታቸው ተሰምቷል። በርግጥም ሊቀ ጳጳሱ እንዲህ ካደረጉ ጳጳሳት የሥራ መልቀቂያ የሚያስገቡበት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ሳይሆን በፓትርያርክና በሴት ወይዘሮዎች ብቻ የሚመራ ቤተ ክህነት ይፈጠራል ማለት ነው።
አንድ አስተያየት ሰጪ እንደተናገሩት የፊታችን ሰኞ ስብሰባ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ስብሰባው የተጠራው በቅዱስ ፓትርያርኩ ከመሆኑ አንጻር ምንም ተለየ ነገር አይጠበቅም። ቅዱስነታቸው የፊታችን እሑድ በዓለ ሲመታቸውን እንደሚያከብሩ ይታወቃል።
ለማንኛውም ደጀ ሰላም በበኩሏ “ተስፋ አንቁረጥ፣ እግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነውና” ትላለች። ቸር ወሬ ያሰማን፣
Source:- ደጀ ሰላም
Related Story:- ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔው ላይ ሳይፈርም ቀረ፤ ጋዜጠኛው ተደበደበ
ደጀ ሰላም:
• የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዘጋቢ ተደበደበ፣
ትናንት ውሳኔ በማሳለፍና ቃለ ጉባዔ በማጽደቅ ስብሰባውን የበተነው ቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ጉባዔው ላይ በመፈራረም ተግባራዊ ያደርጋል ተብሎ ሲጠበቅ ያንን ሳያደርግ ቀረ። ስብሰባው ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ተጨባጭ ውሳኔ ሳያልፍ ቀርቷል። ቅዱስነታቸው በበኩላቸው ቅ/ሲኖዶስ ያዋቀረውንና እርሳቸው ያገዱትን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን እግድ በማንሣት ነገሮችን እንዲያቀዘቅዙ በድጋሚ ቢጠየቁም አሁንም አሻፈረኝ ብለዋል። ይልቁንም አዲስ ሕግ ለራሳቸው ያወጡ ይመስል “የፓትርያርክ ትዕዛዝ በፓትርያርክ ብቻ ነው የሚሻረው” በሚል ከቅዱስ ሲኖዶስ በላይ መሆናቸውን አሳይተዋል። ቅዱስ ሲኖዶስ ሐሳቡን ቀልብሶ ስለ ጉዳዩ እንደገና እንዲነጋገር ያስገደደው ውስጣዊ ጉዳይ ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም። በርግጥ ትናንት ጉባዔው ሲበተን የዚህ ሁሉ ድራማ ዋና ተዋናይ የሆኑት ወ/ሮ እጅጋየሁ ጳጳሳቱን ሲያስፈራሩ እንደነበር ታውቋል። ሴትዬዋ እንዴት ከሕግ በላይ ሊሆኑ እንደቻሉ ለብዙዎች ግራ የሚያጋባ ነገር ሆኗል።
በተያያዘ ዜና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባልና የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የፌዴራል ፖሊስ ልብስ በለበሱ ሰዎች ጥበቃ በቤታቸው ተገድበው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገልጸዋል። እገታው ለክፋት ይሁን ወይም እርሳቸውን ከክፉ ነገር ለመጠበቅ እስካሁን የታወቀ ነገር ለም። ምንጮቻችን እንደተናገሩት አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሳይቀሩ ሊቀ ጳጳሱን ያገተው ክፍል ማን እንደሆነ እንደማያውቁ ተናግረዋል ተብሏል። በቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ በመንግሥት ባለሥልጣናት በኩል አንድና ወጥ የሆነ አቋም እንደሌለ ይታወቃል። የኢሕአዴግ ክፍል የሆነው ሕወሐት በለዘብተኝነት፣ የአማራው ክፍል ክንፍ ነው የሚባለው የነበረከትና ተፈራ ዋልዋ ቡድን ደግሞ በፀረ-ቤተ ክርስቲያንነት ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸው ይታወቃል። የብአዴን አመራሮች ቤተ ክርስቲያኒቱን እንዲህ የሚጠሉበትና የሚያዋርዱበት ምክንያት ግን አሁንም ግልጽ አልሆነም። በቅርቡ በደሴ የቅድስት አርሴማን ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት የተንቀሳቀሱ ምእመናን የፖለቲካ ስም ተሰጥቷቸው ጥቃት እንደደረሰባቸው ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቤተ ክህነቱ አካባቢ በመካሄድ ላይ ያለውን ውጣ ውረድ ከመጀመሪያው ጀምሮ በማቅረብ ላይ የሚገኘው የአማርኛ ጋዜጣ “አዲስ ነገር” ሪፖርተር ስብሰባውን ለመከታተል ከሄደበት ከቤተ ክህነት ወደ ቢሮው ሲመለስ መንገድ ላይ አድፍጠው በጠበቁት ሰዎች መደብደቡ ታውቋል። ጋዜጠኛው “አብርሃም በጊዜው” አንድ ሰው ቀኑን ሙሉ ይከታተለው እንደነበረ ከተገነዘበ በሁዋላ መንገዱን ቀይሮ ወደ ቢሮው ለመግባት ሲሞክር ከፊት አድፍጠው ይጠብቁት በነበሩ ሰዎች በብረትና በብረት ቦክስ መደቆሱ ተገልጿል። ጋዜጠኛው የሕክምና ርዳታ ካገኘ በሁዋላ በደህና ሁኔታ ላይ ይገኛል። ከዚህ በፊት ያልታወቁ ሰዎች የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤትና ዋና አዘጋጅ የሆነውን አማረ አረጋዊን በዚሁ መልኩ መደብደባቸው ይታወሳል።
Sorce:- ደጀ ሰላም
Trackback address for this post
Trackback URL (right click and copy shortcut/link location)
4 comments
lzehima alem mechi anesechin bewunet lehulachinim masitewalun yisten yihinnm yemilew mtsaf silalebigne sayihon mehon mehon mehon yalebetin new /
This post has 11 feedbacks awaiting moderation...